ሚስጥሯ ምን ይሆን
ብለው ቆነጃጅት ይገረማሉ።
'እንደኛ አይደለች
በምን አንደኛ ሆነች?
እንዴት ትበልጠናለች?
ፉንጋ ናት።
ችቦ አይሞላም ወገቧ አይዘፈንላት።
ዳጎስ ያለች ናት።'
ይመስላቸዋል የምዋሻቸው
ሚስጥሩን ስገልጥላቸው ።
የደም ገምቦነቴን እመሰክራለሁ።
እንደዚህ እላለሁ።
የግዛቴ ስፋት አለው ጥልቀት ።
የዳሌዎቼ ቅርፅ ላየው ብሎ ትክ:
እንኳን ተራውን ጀግኖችን የሚያንበረክክ።
አረጋገጤ ዕግር አጣጣል አረማመዴ ።
'ስሙልኝ ጉዴን ቆሜ ሳያት ፈዝዤ ቀረሁ እንዴ? '
ድምፅ ሳላሰማ ቃላት ሳልደረድር:
ፈገግ ስል ልብ የምሰቅል።
ሴት ነኝ።
ምርጥ የነጠርኩ!
ድንቂቱ!
ይህ ሁሉ ማለት
እኔ ነኝ።
ጫጫታ የሞላው ክፍል
በድንገት ስገኝ: ፀጥ ረጭ ይላል።
ንግሥቷ መጣች የተባለ ይመስል ።
ሳልገፋቸው ይወድቁልኛል።
ሳልጠይቃቸው ይነሡልኛል።
ሳላናግራቸው ይመልሱልኛል።
በቀፎ እንዳለ የንብ መንጋ:
ሁሉም ወደኔ የሚንጋጋ!
ለዚህ ነው እላለሁ።
ከዓይኖቼ የሚፈልቀው የፍቅር ብርሃን:
የጥርሶቼ ብልጭታ ያቀልጣል ልብን።
ስንቀሳቀስ የምፈጥረው የወገብ ውዝዋዜ:
ስሜትን ኮርኳሪ ያስረሳል ትካዜ።
የዕግሮቼ ዳንኪራ ያሰኛል ጭፈራ!
እንስት ነኝ።
ድንቂቷ!
ምርጧ!
እኔ ነኝ።
ወንዶቹም ይወራረዱብኛል።
ግን ምኗ ስቦን የምንፍረከረከው?
ላሳያቸው ስሞክር
እኔነቴን በፍቅር:
ይደናገራቸዋል።
ይቸግራቸዋል።
እኔም እላለሁ መስህቤ ያለው:
ውበቴ ያለው:
ወገብ። አሰባበቄ:
አማላዩ ፈገግታዬ።
የልቤ ትርታ
ጡቶቼን ከፍ ዝቅ እያደረገ ከበሮ ሲመታ:
ይመስላል ትዕይንት ይመስላል ጨዋታ!
ያለኝ ግርማ ሞገስ
መንፈስን የሚያድስ:
ይህ ሁሉ ማለት እኔ ነኝ።
ድንቋ! ውቧ!
ምርጧ!
እኔ ነኝ።
አገኛችሁኝ አይደል? ተረዳችሁኝ መሰል።
በማንነቴ የምኮራ! ጠንካራ መንፈሴ የማይታበል።
ጮኬ ሣልጣራ አለሁ አለሁ ሳልል።
ባጠገባችሁ አለፍ ገደም ስል።
ቀልብን የሚገዛው የሚታየው ምስል።
ያስከብራል ያኮራል።
እኔም እላለሁ።
አካሄዴ ሰበር ሰካ
ሣይሆን: በዕርጋታ የተለካ።
ፀጉሬ ሳይዘናፈል
ንኩኝ ንኩኝ የሚል።
እንከባከባለሁ ሁለመናዬን ።
ጣቶቼን አድርጌ ተገን ።
እናም እላለሁ።
እንስት ነኝ።
ምርጧ!
እንስት ነኝ።
ድንቋ!
እኔ ነኝ።
መጋቢት ፪፮ ቀን ፪፻፰
A sweet poem.I raise my hat for you Embet.