'Quite Sure' Poem by Yohanes Jemaneh

'Quite Sure'

ልክ ነህ


መዘምራን ዐለም
መዘምራን ኣርያም
በኪን በነቢቡ
የበዛው ጥበቡ
አንድ ሆነህ ዕልፍነት
ያልተጫነህ ግዝፈት፡፡

ምሑር ሲዶለዱም
ከያኒ ሲያገድም
ባላየ ባልሰማ
ያልበሰለ አዕምሮ
ወንበሩን ሲጫማ፤

አንድ ሰው ይጮኻል አገሬን እያለ
በዘመኑ መክፋት ልቡ እንደቆሰለ፡፡

ለዚያ ለኪነት ሰው
አገሩ ፍቅሩ ናት
እትብቱ ማተቡ
የመኖር ሰበቡ
የኅላዌ ግቡ፡፡

ለፍቅር ያዜሙ ድንበር ሲሻገሩ
አገሬን እያለ ማደሩ ባገሩ
ከጥቅም የፀዳ ፣ ሥሜት የገደለ
የኪን ወዙን ጨምቆ አገሩን የኳለ
ይህ ዜመኛ እንደሆን ብዙሐኑ ያውቃል
ዜማውን ያደምቃል፡፡

ጥቂት ልቃቂቶች ክር የሚስባቸው
ባዘቶው ውል አጥቶ የማጠንጠኛቸው
ስሙን ያጎድፋሉ ግብሩን ባያውቁትም
ደግነቱ እናቴ ካልተዳመጠ ጥጥ ጥብቆ አትጠቅምም፡፡

በዘመን አዙሪት ትናንት የሚኖሩ
ባልቦ ጩኸት ድምጸት እንዳልደነቆሩ
ዜማ-አልባ በማለት ከያኒውን ጠሩ፡፡

መሥዋዕትነት ጥጉን ያላወቁ ቀሩ
በኪን ስም ነግደው ስሙን መጥራት ፈሩ፡፡

ይህ ሁሉ ግሪንቢጥ ባንድ ወንዝ ከበቀለ
አገሩ እንዲቀና ወዙን የገበረ
ባዋቂ ዐላዋቂ እየተወገረ
በምን ድጋፍ ትቁም አገር በኹለት እግሯ
ያለማት እግሯ ሥር አጥፊው ከግንባሯ
ከተደለደሉ፡፡

በርግጥ ብለኸዋል ከበድ ያለ ሰው ነው ቀለል አርጎ የሚኖር፤
ያላዋቂን ስድብ፡ ከዘለፋ የማይቆጥር
ዛሬም የሚደንቀኝ ይሔ ስብእና
የከፍታው ግዝፈት ከማማ አሻቀበ
ኮሽ ባለ ቁጥር እንዳልተሰደበ
ይቅር ባይነትን ካምላኩ ተማረ
ንቆ መተውን ግን እንዴት ልቡ አኖረ? ?
ለዘመኑ የጥበብ ኮከብ እጅ መንሻ

Tuesday, June 13, 2017
Topic(s) of this poem: right
POET'S NOTES ABOUT THE POEM
I wrote this poem to praise Teddy Afro, the most outstanding musician of my motherland. I wrote the poem in my mother-tongue, I will translate it into English in the near future.
COMMENTS OF THE POEM
READ THIS POEM IN OTHER LANGUAGES
Close
Error Success