X-Mass Gift Poem by Yohanes Jemaneh

X-Mass Gift

ጌታ ሆይ!
የሰው ልጅን ሥቃይ ድካም እንግልቱን
በሕይወት ስንክሳር ባክኖ መታከቱን
በሳጥናኤል ሸክም ጫንቃው መጎዳቱን
እጅግ መመረሩን ዐይተህ፡ ተገንዝበህ
የልቡን ተረድተህ
ሥቃዩን ልትሽር፡ ድካሙን ልቀንስ
ሸክም የጎዳውን ጫንቃውን ልታድስ
የሰይጣንን ትብትብ ውሉን ልትሰርዝ
ደብዳቤውን ልትቀድ፡ ትንቢትህ ሊፈጸም
ቃልም ሥጋ ሊሆን ፀሐይ ልትወጣ
ዙፋንህን ትተህ ወደ ዓለም ስትመጣ
አንድ ቃል ነበረኝ፡
በሕገ - ልቦናም በሕገ - ዖሪት
በሐዲስ ኪዳን ቢሆን ባዲሱ ምሪት
ሳመልክህ እንደኖርሁ በጾም በጸሎት
ትልቅ ተስፋ ነበር የልቤ ምኞት
የመንፈስ አምላኬን በሥጋ ማየት፤
አቤቱ ጌታ ሆይ፡
ተስፋዬ እንዲሰምር ምኞቴ እንዲፈጸም
መዝሙር ሲያስተጋባ ከዚያች ቅድስት አገር ከዚያች ቤተልሔም
ፈቅደህ ቢሆን ኖሮ አንተን እንድጎበኝ
ያኔ ስትወለድ ከጎንህ እንድገኝ
ምነው ከእረኞቹ አንዱን ባደረግኸኝ፡፡

መ ል ካ ም ገ ና!

X-Mass Gift
Wednesday, January 6, 2016
Topic(s) of this poem: christmas
POET'S NOTES ABOUT THE POEM
It is an amharic poem just encircled with idea of X-mass.And written last year.
COMMENTS OF THE POEM
Alem Hailu G/kristos 08 January 2016

Dear Yohannes Jemaneh I wish I were one of the Shepherds to witness the birth of Christ, the incarnation of God out of love for man! you have written an interesting poem a timely one

0 0 Reply
Yohanes Jemaneh 09 January 2016

It was just longing the passive and it was my big wish if it would happened. Anyway, I'm glad to see your recognition. Thank you.

0 0
READ THIS POEM IN OTHER LANGUAGES
Yohanes Jemaneh

Yohanes Jemaneh

Ethiopia
Close
Error Success