ወታደር Poem by Dereje Amera

ወታደር

መስዋአት የሆነው
ህይወቱን ሳይሳሳ ሚገብር ለሀገር
ነገ ሚባል የለው ዛሬን ብቻ ሚያድር
ህዝብ በሰላም ወጥቶ በደህና ሚገባው
ወታደር ሲኖር ነው መከታና ጋሻው
እርሱ እኮ ጀግና ነው ማነው የሚተካው
ማነውስ ከእርስዋ ጋር የሚስተካከለው
ሀገር ሚኖረው ሚቀጥለው ህይወት
ክብርን ይገባዋል ለሆነው መስዋአት፤

POET'S NOTES ABOUT THE POEM
Please enjoy my poems in Amharic
COMMENTS OF THE POEM
READ THIS POEM IN OTHER LANGUAGES
Close
Error Success