አልቦ ዐለም
አበባ ቢሰጡ አብሮነት ካልፈካ
ቀለበት ቢያደርጉ ጣት ካልተነካካ
ሽቶ ቢያስታጥቡ ፍቅር ካላወደ
ልብን ቢያስረክቡ ልብ ካልወለደ
በውነተኛ ሥሜት ወዳጅ ከቀለደ
ካልተወራወሩ በናፋቂ ቃላት
ካልተከራከሩ በመውደድ ጣር ቅናት
ካልተደማመጡ ባይን ላይን ንበት
ያብሮ መሳቅ ዜማ ጆሮ ካልዘራበት
የፈገግታ ጮራ ቀለም ካልደፋበት
ጥምረት ካላኖረ የተስፋ ጉልላት
ምን ይሉት ነው መውደድ
ምን ይሉት ነው ማጣት
የብቻነት ዐለም ስለምን ያሰጋል
በነጠላ ጉዞ ነፃ ዐየር ያስምጋል
በሰለለች ዕድሜ ማፍቀር ምን ያደርጋል?
This poem has not been translated into any other language yet.
I would like to translate this poem