Desperation Poem by Yohanes Jemaneh

Desperation

ነበረ ስላንቺ ሐሣቤ ሚቀና
ብዕሬ ሚሠላ
እብሪት ያደደረው ልቤ የሚላላ
ናፍቆት የደቆሰው ውስጤ የሚንሰራራ
ጭንቀት የተጣባው መንፈሤ የሚገራ
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡[-]✿✿✿፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ዛሬ ግን ተረሳኝ ለፍቅርሽ ያዜምኩት
ግጥሙ ተዘነጋኝ በቃሌ የያዝኩት
ቅላፄውም ጠፋኝ ዳዊቴ ያረኩት
መራቅሽ ሲቀመር፡ ተስፋዬ እየሳሳ
በፍቅርሽ መቁረጡን አስጨከነኝሳ
(ላም አለኝ በሠማይ አሳሰበኝሳ)
አንቴናውን ያጣ ቢራቢሮ ሳለሁ
አበባው ላይ ማረፍ እንዴት እችላለሁ?

Thursday, October 27, 2016
Topic(s) of this poem: rhyme
POET'S NOTES ABOUT THE POEM
despair on timeless thought
COMMENTS OF THE POEM
READ THIS POEM IN OTHER LANGUAGES
Close
Error Success