ለልቤ ላይ ጀግና
ሰው አገርን ቢያክል ለምን ይደንቀኛል
በሺህ ዘመን አንዴ ይህ እውነት ይገኛል
ልክ እንደኔ ንጉሥ መንፈሥ የሚያቀና
በኩራት ‘ሚጠሩት የልብ ላይ ጀግና
ተፈጥሮ አይቻለሁ ልከኛ ስንዱ
አገርን ከመንደር አጣርቶ መውደዱ
ድንበርን ልማጥበቅ ነቅቶ መማለዱ
የብርሐን ዘመንን ፈጥኖ መዋጀቱ
ጊዜን ተፈናጦ በወኔ መግራቱ
እንቅፋት ሳይገታው ሕልሙን መመተሩ
መስዋእት ሆኖ ቆሞ ለዛሬው አገሩ
እንዲህ ነው አርአያ እንዲህ ነው ግንባር ሰው
እየሞቱ መቆም ዘመን የተዋሰው
እርሱ ስመ ግዙፍ እርሱ ስመ ጥሩ
ጨለማ እየገፉ አይኖቹ የሚያበሩ
ስለናት አንድ ሰው ስለአገር ብዙነት
መምሕርስ እርሱ የተግባር ሰውነት
ብቻ መቆም ብርታት በማያልቀው ጽልመት
በርግጥ አለው ምርኩዝ ግራና ቀኝ እጁ
ከመሐል ልቡ ላይ የምትዋብ ቅንጁ
ቆቅ አባቱን መሳይ ዐለምማያ ልጁ
እኒህ ናቸው እሱ ከሕልሙ ለጥቆ
ፍልስፍና ኪሱ መሻትን አጥብቆ
ለሁሉ ልክነት አስታቅፎት በልቡ
በባዶ እግር ቆሞም ጠፈር ነው ምናቡ!
አንድ ሰው አንድ አገር! ልብ ጠቦት ምድር
እንዴት አገር ሰውን ያክላል እላለሁ
እስከዛሬ ድረስ ገርሞኝ ጠይቃለሁ፡፡
ተጻፈ በ30/6/2013 ዓ.ም
ለንጉሠነገሥት ዳግማዊ ቴዎድሮስ ዘ ኢትዮጵያ
This poem has not been translated into any other language yet.
I would like to translate this poem