ትውስታ
የሮጥንበት ቀዬ
ያወራነው ዘዬ
የታጠፍነው ቅያስ
ያማተርነው ዐድማስ
የሳቅንበት ተረክ የሞላው ፍሠሐ
የተናበብንበት ያይን ጥቅሻው ሁላ
ዘመን ይናፍቃል
ሕይወት ይናፍቃል
ትዝታ ይሠርቃል
ስቀው ያሳለፉት
በፈገግታ ጠርተው
በኩርፊያ የሸኙት።
This poem has not been translated into any other language yet.
I would like to translate this poem